የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው

By Melaku Gedif

December 16, 2024

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቱርክ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ሥራ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው፡፡

ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን በፈረንጆቹ 2025 የመጀመሪያ ወራት በኢትዮጵያና ሶማሊያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ማቀዳቸውን አስታውቀዋል፡፡

ጉብኝቱ ኢትዮጵያና ሶማሊያ በፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን አደራዳሪነት የሰላም ስምምነት መፈራረማቸውን ተከትሎ የታቀደ ነው ተብሏል፡፡