የሀገር ውስጥ ዜና

በዶዶላ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ12 ሰዎች ሕይወት አለፈ

By Melaku Gedif

December 16, 2024

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ወረዳ ኤዶ ከተማ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የ12 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

አደጋው ሁለት በተቃራኒ መስመር ሲጓዙ ከነበሩ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች አንዱ የአህያ ጋሪን ለማትረፍ ሲሞክር በመጋጨታቸው የተፈጠረ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተከሰተው አደጋም እስካሁን የ12 ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን÷ በ19 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል ጉዳት መድረሱን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡