የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ከኡጋንዳ ህዝብ መከላከያ ሃይል ጠቅላይ አዛዥ ጋር ተወያዩ

By Meseret Awoke

December 16, 2024

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 7፣ 2017 ((ኤፍ ኤም ሲ)) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኡጋንዳ ህዝብ መከላከያ ሃይል ጠቅላይ አዛዥ ጀነራል ሙሆዚ ካይኔሩጋባ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጀነራል ሙሆዚ ካይኔሩጋባ ጋር ዛሬ ማለዳ ተገናኝተው መመምከራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡