ስፓርት

አትሌት ሱቱሜ ከበደ በኮልካታ የ25 ኪሎ ሜትር ውድድር አሸነፈች

By Feven Bishaw

December 16, 2024

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሱቱሜ ከበደ በህንድ የተካሄደውን የኮልኮታ የ25 ኪሎ ሜትር  ውድድር በበላይነት አጠናቀቀች።

 

አትሌቷ ውድድሩን 1፡19፡17 በሆነ ሰዓት በመግባት ቀዳሚ ሆናለች።

 

አትሌት ሱቱሜን በመከተል ኬንያዊቷ አትሌት ቼፕንግኖ በ1፡19፡44 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ ሆና ስታጠናቅቅ፤ ባህሬናዊቷ አትሌት ጂሳ ድሞ በ1፡21፡29 በሆነ ሰዓት ሶስተኛ ሆና ማጠናቀቅ ችላልች።

 

ውድድሩ ሊካሄድ ሁለት ሳምንት ሲቀረው እንደምትሳተፍ ያረጋገጠችው ሱቱሜ ከሆድ  ህመም አገግማ ይህን ውጤት ማስመዝገቧ ተነግሯል።