አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የታንዛኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር መሃሙድ ታቢት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
መሃሙድ ታቢት በነገው ዕለት በአዲስ አበባ በሚጀመረው የኢትዮ- ታንዛኒያ የጋራ የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ነው አዲስ አበባ የገቡት፡፡
ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡