የሀገር ውስጥ ዜና

በታላቁ ህዳሴ ግድብ የተያዘው ውሃ በመጭው አመት በ2 ተርባይኖች ሀይል ማመንጨት ያስችላል – ኢ/ር ስለሺ በቀለ

By Tibebu Kebede

July 22, 2020

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በታላቁ ህዳሴ ግድብ የተያዘው ውሃ በመጭው አመት በ2 ተርባይኖች ሀይል ማመንጨት እንደሚያስችል የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ገለፁ።

ሚኒስትሩ ኢንጅነር ስለሺ በቀለ የታላቁ የህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት መጠናቀቁን አስመልክቶ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

ኢንጅነር ስለሺ ሐምሌ 12 ቀን 2012 ዓ.ም ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ የህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ አመት ሙሌት ተሳክቷል ነው ያሉት።

ግድቡ የሚያስፈልገውን የመጀመሪያ ዙር 4 ነጥብ 9 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ በመያዝ ከግድቡ አናት ላይ ፈሷል ያሉት ሚኒስትሩ ይህም የተሳካው ወደታችኛው ተፋሰስ የሚሄደው ውሃ ሳይቋረጥ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ይህ ውጤትም ዋነኛ ምዕራፍ መሆኑን በማንሳት በግድቡ የተያዘው ውሃ በመጭው አመት በ2 ተርባይኖች ሀይል ማመንጨት እንደሚያስችል እና ግንባታው እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል።