የሀገር ውስጥ ዜና

በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር መከላከል ልምድ ለመለዋወጥ የሚያስችል ውይይት ተካሄደ

By yeshambel Mihert

December 18, 2024

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፌደራል ፖሊስ ከጣሊያን ደኀንነት ሚኒስቴር ጋር በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር መከላከል፣ በፎረንሲክ ምርመራ እና በኮስት ጋርድ ፖሊስ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂዷል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል እና የጣሊያን የሀገር ውስጥ ደኀንነት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የዓለም አቀፍ ግንኙነት ሚኒስትር አማካሪ ኢፎሚያ ኤስፖሲቶ በበይነ መረብ ተወያይተዋል።

በውይይቱም ከጣሊያን ስቴት ፖሊስ ጋር በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር መከላከል ኦፕሬሽን፣ በድንበር ቁጥጥር፣ በቁሳቁስ ድጋፍ፣ በፎረንሲክ ምርመራ እና በኮስት ጋርድ ፖሊስ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ለፖሊስ አመራርና አባላት የትምህርት ዕድል እና የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በፈረንጆቹ መጋቢት 2025 በጣሊያን ሀገር እንዲሰጥ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የፌደራልፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡