የሀገር ውስጥ ዜና

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የኔትወርክ አገልግሎቱን በጋምቤላ ከተማ አስጀመረ

By Meseret Awoke

December 19, 2024

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የደንበኞች የኔትወርክ አገልግሎት በጋምቤላ ከተማ በይፋ አስጀምሯል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ በማስጀመርያ መርሐ – ግብሩ ላይ ሳፋሪ ኮም ተደራሽነቱን በማስፉት በጋምቤላ የላቀ የቴሌኮም ኔትዎርክ እንዲኖር በማሰብ የማስጀመርያ መርሐ -ግብር መከናወኑን ገልጸዋል፡፡

የኔት ወርክ አገልግሎቱ መጀመር የቢዝነስ እንቅስቃሴዎችን የማሳለጥ፣ ኢንቨስትመንትን መሳብ፣ የስራ ፈጠራን የማሳደግና ሌሎች በርካታ ፋይዳዎች እንደሚኖሩት መጥቀሳቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የሳፋሪም ኢትዮጲያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዊም ቫን ሂለፑት በበኩላቸዉ ÷ዛሬ በጋምቤላ ያስጀመርነው የኔትዎርክ አገልግሎት በመላው ኢትዮጵያ ተደራሽነታችንን ለማስፋትና በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ማህበረሰቦችን ለማስተሳሰር ያለንን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ብለዋል።