የሀገር ውስጥ ዜና

ፀጋዎችን አሟጦ በመጠቀም ከተረጂነት ለመላቀቅ መረባረብ ይገባል – አቶ ጥላሁን ከበደ

By Feven Bishaw

December 19, 2024

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ ፀጋዎችን አሟጦ በመጠቀም ከተረጂነት ለመላቀቅ መረባረብ ይገባል ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ተናገሩ።

“ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነትና ክብር” በሚል መሪ ሃሳብ በአርባምንጭ ከተማ ውይይት እየተካሄደ ነው።

መድረኩ በክልሉ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ነው ተብሏል።

በመድረኩ ርዕሰ መስተዳድሩ÷ ዓመቱን ሙሉ የሚፈሱ ወንዞች እና ያለንን ለም መሬት በመጠቀም ከተረጂነት ለመላቀቅ መትጋት ይገባናል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይለማሪያም ተስፋዬ በበኩላቸው÷ የክልሉን የምግብ እጥረት በመቅረፍ ምርታማነትን ለማሳደግ ቢሮው ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።