የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ አደም ፋራህ በባሕር ዳር የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ

By amele Demisew

December 20, 2024

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ በባሕር ዳር ከተማ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸውም ጣና ዳር የሚገኘውን የጣና ማሪና ሪዞርት ግንባታ ሒደት ጨምሮ የባሕር ዳር ከተማ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ያለበትን ደረጃ ተመልክተዋል።

በጉብኝት መርሐ ግብሩ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡

በደሳለኝ ቢራራ