ስፓርት

ዋሊያዎቹ የቻን የመልስ ጨዋታቸውን ከሱዳን አቻቸው ጋር ያደርጋሉ

By ዮሐንስ ደርበው

December 25, 2024

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) የመጨረሻ ዙር ማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን ዛሬ ከሱዳን አቻው ጋር ያደርጋል፡፡

የሁለቱ ቡድኖች የቻን የመጨረሻ ዙር ማጣሪያ ጨዋታ 11 ሠዓት ላይ በሊቢያ ቤንጋዚ ቤኒና ማርትየርስ ስታዲየም ይደረጋል።

ብሔራዊ ቡድኑ በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ በሱዳን 2 ለ 0 መሸነፉ ይታወሳል፡፡