የሀገር ውስጥ ዜና

የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ ተጠናቀቀ

By ዮሐንስ ደርበው

December 25, 2024

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቀቀ፡፡

በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች እና በልዩ ልዩ የፓርቲ አጀንዳዎች ላይ ሲመክር የቆየው የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ አመሻሽ ላይ ስብሰባውን አጠናቅቋል፡፡

ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ከውይይቶቹ በመነሳት የተለያዩ ውሳኔዎች ማስተላለፉን እና አቅጣጫዎች ማስቀመጡን የፓርቲው መረጃ አመላክቷል፡፡