የሀገር ውስጥ ዜና

ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ500 ሺህ ህሙማን አገልግሎት ሰጠ

By Melaku Gedif

December 26, 2024

አዲስ አበባ፣ ታህሣሥ 17 ፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ 500 ሺህ ለሚሆኑ ህሙማን የህክምና አገልግሎት መስጠቱ ተገለጸ።

ሆስፒታሉ ውስብስብ የቀዶ ህክምና፣ ተመላለሽ ህክምና፣ የተኝቶ ህክምናን ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለኢትዮጵያ ህዝብ ተደራሽ ማድረጉ ተነግሯል።

በተጨማሪም ሆስፒታሉ በክረምት የጤና በጎ አገልግሎት ለሶስተኛ ጊዜ “እሺ ለበጎ ተግባር” በሚል መሪ ሀሳብ አገልግሎት መስጠቱን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መረጃ አመላክቷል።