የሀገር ውስጥ ዜና

ፊንላንድ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ እንደምታጠናክር አስታወቀች

By ዮሐንስ ደርበው

December 27, 2024

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፊንላንድ በትምህርት መስክ ለኢትዮጵያ የምታደርገው ትብብርና ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጣለች፡፡

የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ አየለች እሸቴ በኢትዮጵያ የፊንላንድ አምባሳደር ከሆኑት ሲኒካ አንቲላ ጋር በሁለትዮሽ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ተወያይተዋል፡፡

በዚሁ ወቅት የፊንላንድ መንግሥት በትምህርቱ መስክ በተለይም በልዩ ፍላጎት ትምህርት እያደረገ ላለው ድጋፍ ያመሰገኑት ሚኒስትር ዴዔታዋ÷ ትብብሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

አምባሳደሯ በበኩላቸው በሀገራቱ መካከል በትምህርት መስክ ያለው የሁለትዮሽ ትብብር እያደገ መምጣቱን ጠቁመው በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡