የሀገር ውስጥ ዜና

የቁሉቢ ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በድምቀት ተከብሮ ተጠናቀቀ

By Melaku Gedif

December 28, 2024

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቁሉቢ ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በድምቀት ተከብሮ መጠናቀቁን የፀጥታ ጥምር ኃይል አስታውቋል፡፡

ግብረ ሃይሉ በዓሉ በስኬት እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ትብብር ላደረገው የአካባቢው ህብረተሰብ፣ ለኃይማኖት አባቶች፣ ለአስተዳደር አካላት እንዲሁም የተሰጣቸውን ተልዕኮ በሚገባ ለተወጡት የፀጥታ አካላት አመራርና አባላት ምስጋና አቅርቧል፡፡

በዓሉን አስመልክቶ የተቋቋመው ጊዜያዊ ችሎት በሞባይል እና በጫማ የስርቆት ወንጀል የተከሰሱ ግለሰቦች ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ማስተላለፉም ተጠቁሟል፡፡

በዚህም ወንጀለኞቹን ያስተምራል ሌሎችን ያስጠነቅቃል በማለት አንድ ዓመት ከአራት ወር እስከ አንድ ዓመት ከሁለት ወር የሚደርስ የፍርድ ውሳኔ ማስተላለፉን የፌዴራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡