የሀገር ውስጥ ዜና

በጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ ጅቡቲ ገባ

By Melaku Gedif

December 28, 2024

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ ዛሬ ማምሻውን ጅቡቲ ገብቷል።

የልዑካን ቡድኑ አባላት ጅቡቲ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሃመድ አሊ የሱፍ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ልዑካኑ በጅቡቲ ቆይታቸው ከተለያዩ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ጋር ይመክራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡