አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከነገ ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት በዘመቻ መልክ እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ጤና ቢሮ አስታወቀ።
ክትባቱ የሚሰጠው ዕድሜአቸው ከ9 እስከ 14 ዓመት ለሆኑ ከ177 ሺህ 900 በላይ ሴቶች መሆኑ ተገልጿል፡፡
በሁሉም የመንግሥት እና የግል ትምህር ቤቶች እንዲሁም ከትምህርት ቤት ውጪ ባሉ ቦታዎች ክትባቱ ይሰጣል መባሉን የቢሮው መረጃ አመላክቷል፡፡
በኢትዮጵያ ከጡት ካንሰር ቀጥሎ ለሕብረተሰቡ ከፍተኛ የጤና ስጋት መሆኑ እና በገዳይነቱም በ2ኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡