የሀገር ውስጥ ዜና

ለወሊድ አገልግሎት የሚውሉ 370 አምቡላንሶች ለክልሎች ተሰጡ

By Feven Bishaw

January 02, 2025

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጤና ሚኒስቴር ለወሊድና ድንገተኛ ሕክምና አገልግሎት የሚውሉ 370 አምቡላንሶችን ለክልሎች አስረክቧል።

በርክክብ ሥነ ሥርዓቱ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ፣ሚኒስትር ዴኤታዎች እና የክልል ጤና ቢሮዎች ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

አምቡላንሶቹ በወሊድና ድንገተኛ ሕክምና አገልግሎት ዘርፍ የሚስተዋለውን ውስንነት መቅረፍ ያስችላሉ ተብሏል።

በመላኩ ገድፍ