የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ አዳነች ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች ጋር ተወያዩ

By Meseret Awoke

January 16, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሉት ፥ የጥምቀት በዓል የተለመደውን ሃይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር ለማድረግ ከሃይማኖቱ አባቶች ጋር ተወያይተናል፡፡

ሁላችንም በዓሉ ሃይማኖታዊ እሴቱን እና የቱሪስት መስህብነቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር ተባብረን በጋራ እንስራ ሲሉም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል::