አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 944 ሚሊየን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ 97 አልሚዎች አዳዲስ ፈቃድ መሥጠቱን የጋምቤላ ክልል ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ሉ ኦቡፕ (ዶ/ር) ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በግብርና ዘርፍ 476 ሚሊየን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ 72 አልሚዎች ፈቃድ ተሰጥቷል፡፡
እንዲሁም በአገልግሎት ዘርፍ 435 ሚሊየን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ 20 አልሚዎች ፈቃድ መሰጠቱን ገልጸዋል፡፡
በኢንዱስትሪው ዘርፍ 33 ሚሊየን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ አምስት አልሚዎች ፈቃድ ሰጥተናል ብለዋል፡፡
በዮሐንስ ደርበው