የሀገር ውስጥ ዜና

የጥምቀት በዓል በመላ ሀገሪቱ በድምቀት ተከበረ

By Mikias Ayele

January 19, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እና በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ተከበረ ፡፡

በዓሉ በተለይም በአዲስ አበባ ጃንሜዳ እና በጎንደር የእምነቱ ተከታዮች እና የውጭ ሀገራት ጎብኚዎች በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል፡፡

እንዲሁም በባቱ ደምበል ሐይቅ ደሴቶች እና በምንጃር ሸንኮራ ኢራምቡቲ በድምቀት እየተከበረ ሲሆን በአጠቃላይ የሀገሪቱ ክፍሎች በሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች ነው የተከበረው፡፡

ትናንት የጥምቀት ከተራ በዓል በመላ ሀገሪቱ የተከበረ ሲሆን በዚህም በሃይማኖታዊ ስነ ስርዓት መሰረት ታቦታት ከየአብያተክርስቲያናቱ ወጥተው ወደ የማደሪያቸው ባህረ ጥምቀት ገብተዋል።