የሀገር ውስጥ ዜና

የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ተከበረ

By Mikias Ayele

January 19, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጥምቀት በዓል በአዲስ አበባ ልደታ ማሪያም ካቶሊክ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተከበረ።

በዓሉ የሀይማኖት አባቶች፣ የእምነቱ ተከታዮች ምዕምናንና ሌሎች እንግዶች በተገኙበት በቅዳሴ፣ በፀሎት፣ በዝማሬ፣ በምስጋና እና ሌሎች ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች ነው በድምቀት የተከበረው።

በዓሉ በመላ ሀገሪቱ ባሉ የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያናት እንደተከበረ መገለፁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡