የሀገር ውስጥ ዜና

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ5 ሺህ 600 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ

By Tibebu Kebede

July 25, 2020

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ መስኮች ያስተማራቸውን ከ5 ሺህ 600 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ፡፡

ከተመራቂዎቹ መካከል 244 በሶስተኛ ዲግሪ፣ 3 ሺህ 128 በ2ኛ ዲግሪ እንዲሁም 2 ሺህ 370 በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ ናቸው፡፡

ተመራቂዎቹ ወቅታዊ የጤና ስጋት በሆነው ኮቪድ19 ሳቢያ በቴሌቪዥን እና በዩኒቨርሲቲው ማህበራዊ የትስስር ገጽ በተላለፈ ስነ ስርአት ነው የተመረቁት፡፡