የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ታዬ ጥምቀትን በጎንደር የታደሙ ቱሪስቶችን አነጋገሩ

By Mikias Ayele

January 20, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በጎንደር የጥምቀት በዓልን የታደሙ የውጭ ሀገራት ቱሪስቶችን አነጋግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ባለ ብዙ ቀለም የሆነውነን የጥምቀት በዓል ለማክበር ጎንደር የመጡ ቱሪስቶችን አግኝተው ስሜታቸውን እንደተጋሩ ገልጸዋል፡፡

ቱሪስቶቹ በቆይታቸው በሕይወታቸው የማይረሱትን ትዝታ እንዳሳለፉና በበዓሉ ደስተኛ መሆናቸውን ነግረውኛል ብለዋል፡፡

የጥምቀትን አይነት የአደባባይ በዓላት የኢትዮጵያን ልዩ ታሪካዊና ባሕላዊ እሴቶች የበለጠ እንደሚያጎሉም  ፕሬዚዳንቱ አስገንዝበዋል፡፡