የሀገር ውስጥ ዜና

ጥምቀትና ቃና ዘገሊላ በዓላት በድምቀት ተከብረው ተጠናቀቁ

By Mikias Ayele

January 20, 2025

አዲስ አበባ፣ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጥምቀትና ቃና ዘገሊላ በዓላት በድምቀት ተከብረው መጠናቀቃቸውን የጸጥታና ደኅንነት ጥምር ሃይል አስታውቋል፡፡

ጥምር ኃይሉ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዩኒስኮ ካስመዘገበቻቸው ከማይዳሰሱ ቅርሶች ውስጥ አንዱ የሆነው የጥምቀት በዓል አዲስ አበባን ጨምሮ በመላ ኢትዮጵያ በድምቀት ተከብሮ መጠናቀቁን ገልጿል፡፡

በተመሳሳይ በዛሬው ዕለት የተከበረው የቃና ዘገሊላ በዓል በድምቀት ተከብሮ መጠናቀቁ ነው የተጠቆመው፡፡

በዓሉ በድምቀት እንዲከበር የበኩላቸውን ድርሻ ላበረከቱት አካላት ጥምር ሃይሉ ምስጋና ማቅረቡን የፌዴራል ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡