የሀገር ውስጥ ዜና

ለጋምቤላ ከተማ የ33 ሚሊየን ብር የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ማሽን ድጋፍ ተደረገ

By Melaku Gedif

January 20, 2025

አዲስ አበባ፣ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዓለም አቀፉ የሕፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) 33 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ማሽን ለጋምቤላ ከተማ ድጋፍ አድርጓል፡፡

የክልሉ ውሃና ኢነርጅ ቢሮ ሃላፊ አቶ ኡጁሉ ኡዶል÷ድጋፉ በዘመናዊ መንገድ ደረቅ ቆሻሻን ለማስወገድ የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡

በማሽኑ ደረቅ ቆሻሻን የማስወገድ ሥራን የሚያከናውኑ ባለሞያዎች በዘርፉ እውቀትና አቅም ሊኖራቸው እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

ዩኒሴፍ ከተማው ያለበትን ችግር ተረድቶ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡