አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ የአንጎላ አምባሳደር ከሆኑት ሚጌል ሴሳር ዶሚንጎስ ቤምቤን ጋር የሀገራቱን ግንኙነት በይበልጥ ለማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡
በውይይታቸው ወቅትም በኢትዮጵያና በአንጎላ መካከል ስላለው ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነት ሚኒስትር ዴዔታው አንስተዋል፡፡
አንጎላ የአፍሪካ ሕብረትን ተለዋጭ የፕሬዚዳንትነት ቦታ ስትይዝ የአኅጉሪቱን አጀንዳ በማራመድ ረገድ ጉልህ ሚና እንደሚኖራት መግለጻቸውን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡
አምባሳደር ሚጌል ቤምቤ በበኩላቸው፥ አንጎላ ከኢትዮጵያ ጋር ጠንካራ ግንኙነት እንዲኖራት ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል፡፡
በተጨማሪም ቀጣናዊ ትብብርን ስለማጠናከርና ቀጣዩ አፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ በስኬት እንዲካሄድ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይም መክረዋል፡፡