የሀገር ውስጥ ዜና

ሚኒስትሩ የፋሲል  ቤተ-መንግሥትን ጎበኙ

By Mikias Ayele

January 22, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በጎንደር ከተማ የሚገኘውን የፋሲል ቤተ-መንግሥት ጎብኝተዋል፡፡

ከሚንስትሩ በተጨማሪ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባና የጎንደር ዩንቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አስራት አፀደ ወይን (ዶ/ር) እንዲሁም ሌሎች የመንግሥት ሥራ አመራሮች በጉብኝቱ ተሳትፈዋል፡፡

በቅርቡ ጥገና የተደረገለትን የፋሲል ቤተ-መንግሥት የመንግሥት ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ በርካታ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ቱሪስቶች እየጎበኙት ነው፡፡

በሰላም አስመላሽ