አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኔዘርላንድስ በተለያዩ ዘርፎች ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከረ ቁርጠኛ መሆኗን ገልጻለች፡፡
የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ከኔዘርላንድስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ስቲጅን ጃንሰን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ በሀገራቱ የሁለትዮሽ ትብብር እና በቀጣናዊ ትስስር ጉዳዮች ላይ በትኩረት መክረዋል፡፡
ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)÷በቅርቡ በኢትዮጵያ የተከሄደውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ሒደት አስመልክተው ገለጻ አድርገዋል፡፡
ስቲጅን ጃንሰን በበኩላቸው÷የኢትዮጵያን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጠቃላይ ለውጥ ማድነቃቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
ኔዘርላንድስ ከኢትዮጵያ ጋር በኢንቨስትመንት፣ በልማት፣ በንግድና ሌሎች ዘርፎች ያላትን ትብብር ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗንም አረጋግጠዋል፡፡