የሀገር ውስጥ ዜና

ኤምባሲው የአዲስ አበባ አሽከርካሪ ተሽከርካሪ ባለስልጣን አገልግሎትን አደነቀ

By ዮሐንስ ደርበው

January 22, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አገልግሎት አሰጣጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየዘመነ መምጣቱን የአሜሪካ ኤምባሲ ተወካዮች ገለጹ።

ባለስልጣኑ ለኮር ዲፕሎማቶች የውጭ መንጃ ፈቃድ ቅያሬ፣ የእድሳትና ሌሎች አገልግሎቶችን እየሰጠ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ለዚህ ሲባልም ዲፕሎማቶች የልዩ አገልግሎት የሚያገኙበት አሰራር መዘርጋቱንም ነው ባለስልጣኑ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ ያስታወቀው፡፡

የአሜሪካ ኤምባሲ በዚህ አገልግሎት ተጠቃሚ ከሆኑት ውስጥ አንዱ ሲሆን÷ የኤምባሲው ተወካዮች አገልግሎት አሰጣጡን በተለያዩ ማዕከላት ጎብኝተው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየዘመነ በመምጣቱ መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡

በርካታ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና የ132 ኤምባሲዎች ንብረት የሆኑ ከ11 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎችን መመዝገቡን ባለስልጣኑ አስታውቋል።