አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት ሥድስት ወራት 74 ሺህ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ቱሪስቶች በኢትዮጵያ የሚገኙ ብሔራዊ ፓርኮችን ጎብኝተዋል፡፡
በግማሽ ዓመቱ በአጠቃላይ ከእንስሳት አጠቃቀም ከ62 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ለፋና ዲጂታል አስታውቋል፡፡
ከተገኘው ገቢ 49 ነጥብ 8 ሚሊየን ያህሉ ከዱር እንስሳት ፍጆታዊ አጠቃቀም (ሕጋዊ አደን) መሆኑንም አስረድቷል፡፡
ከኢ-ፍጆታዊ የዱር እንስሳት አጠቃቀም ደግሞ 12 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር መገኘቱን ነው ያስታወቀው፡፡
የተሻለ የጎብኝ ቁጥር ካስተናገዱት ብሔራዊ ፓርኮች መካከል÷ ነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ፣ ባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ፣ ስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ፣ አብጃታ ሻላ ሐይቆች ብሔራዊ ፓርክ እና ሌሎችም እንደሚገኙበት ተጠቅሷል፡፡
በኢትዮጵያ 27 ብሔራዊ ፓርኮች እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡
በዮሐንስ ደርበው