አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቱኒዚያ የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ሂቸም መቺቺ አዲሱ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ተገልጿል።
አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሂቸም መቺቺ በአንድ ወር ውስጥ አዲስ መንግስት የሚመሰርቱ መሆኑንም የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
የ46 ዓመቱ የህግ ባለሙያ ሂቸም መቺቺ በያዝነው ወር መጀመሪያ አካባቢ በራሳቸው ፍቃድ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣናቸውን የለቀቁትን ኤሊየስ ፈከህፋክህን የሚተኩ ይሆናል።
አዲሱ የቱኒዚያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሂቸም መቺቺ በሰጡት መግለጫም፥ የቱኒዚያን ህዝብ ፍላጎት የሚመጥን አዲስ መንግስት ለመመስረት እንደሚሰሩ አስታውቅዋል።
ቱኒዚያ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር የፈነዳውን የአረብ አብዮት ተከትሎ ስኬታማ ዴሞክራሲያዊ ሽግግር በማድረግ ትወደሳለች።
ሆኖም ግን የሀገሪቱ መሪዎች የቱኒዚያ ህዝብን ፍላጎት ለማሟላት ትግል እያደረጉ ቢሆንም፤ አሁን ላይ በዓለም ላይ የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ተከትሎ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ የባሰውኑ ተጎድቷል።
የኮሮና ቫይረስ በሀገሪቱ ከተገሰተ በኋላ በ1 ሺህ 400 ሰዎች ላይ ቫይረሱ የተገኘ ሲሆን፥ 50 ሰዎችም በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን ማጣታቸውም ተነግሯል።
ምንጭ፦ aljazeera.com
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።