የሀገር ውስጥ ዜና

ከምሁራን ጋር የሚደረግ ውይይት የልማት ስራዎችን ለማስቀጠል ወሳኝ መሆኑ ተመላከተ

By Feven Bishaw

January 24, 2025

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከምሁራን ጋር የሚደረግ ውይይት የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ለማስቀጠልና ሰላምን ለማስከበር ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ።

በጅማ ዩኒቨርሲቲ ‘የምሁራን ሚና ለሀገር ግንባታ’ በሚል መሪ ሃሳብ ውይይት እየተደረገ ነው።

በመድረኩ ላይ የውውይት መነሻ ጽሁፍ በምሁራን ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።

በመድረኩ የተገኙት በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ የፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ነመራ ቡሊ፤ በሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት የምሁራን ሚና የላቀ ነው ብለዋል።

በመሆኑም ከምሁራን ጋር የሚደረግ ውይይት የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ለማስቀጠልና ሰላምን ለማስከበር ይረዳል ብለዋል።

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጀማል አባ ፊጣ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ያለውን የሰው ሃብት በማቀናጀት የተፈጥሮ ሃብትን ማልማት ከተቻለ ሀገራዊ ግብን ማሳካት እንደሚቻል ጠቁመዋል።

ምሁራን ስለሃገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው መሰል መድረኮች ወሳኝ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

በሙክታር ጠሃ