የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ 24 ሰዓታት 720 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ14 ሰዎች ሕይወት አልፏል

By Tibebu Kebede

July 26, 2020

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 9 ሺህ 527  የላብራቶሪ ምርመራ 720 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 13 ሺህ 968 መድረሱንም የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ባወጡት መረጃ አመላክተዋል።

ከዚህ ባለፈ የ14 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 223 መድረሱንም አመላክተዋል።

በሌላ መልኩ በትናንትናው እለት 250 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 6 ሺህ 216 መድረሱም ተገልጿል።

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን 382 ሺህ 339 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 13 ሺህ 968 ደርሷል።

አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 7 ሺህ 527 ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 65 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

እስካሁን በኢትዮጵያ 6 ሺህ 216 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገገሙ፤  የ223 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 2 ሰዎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ይታወሳል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።