አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሐረሪ ክልል የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ በኤረር ወረዳ በዛሬው ዕለት ተጀምራል፡፡
“አፈራችን ለሀገራዊ ብልጽግናችን” በሚል መሪ ሃሳብ የሚከናወነው የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራ በክልሉ በሚገኙ ሦስት የገጠር ወረዳዎች ለአንድ ወር እንደሚካሄድ ተገልጿል።
የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተወካይና የክልሉ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሄኖክ ሙሉነህ እንደተናገሩት÷ባለፉት ዓመታት በተሰሩ የተፋሰስ ልማት ሥራዎች ምርትና ምርታማነት መጨመሩን አንስተዋል፡፡
የክልሉ ግብርና ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ነስረዲን አህመድ በበኩላቸው÷የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራው በ16 ተፋሰሶች እና በ900 ሄክታር መሬት ላይ እንደሚከናወን ተናግረዋል፡፡
በአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራውም ከ40 ሺህ በላይ ሕዝብ እንደሚሳተፍ ነው የገለጹት፡፡
በተሾመ ኃይሉ