የሀገር ውስጥ ዜና

ከ4 ነጥብ 2 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈርማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ ደረሰ

By Meseret Awoke

January 26, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) እስከዛሬዋ ዕለት ድረስ 4 ሚሊየን 292 ሺህ 600 ኩንታል አፈር ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ መድረሱን የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡

ለ2017/18 የምርት ዘመን ከውጭ የሚያስመጣው የአፈር ማዳበሪያ እንደቀጠለ መሆኑን ኮርፖሬሽኑ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ አስታውቋል፡፡

ወደብ ከደረሰው ማዳበሪያ ውስጥ 3 ሚሊየን 45 ሺህ 252 ኩንታል ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዞ በኅብረት ሥራ ማኅበራት አማካኝነት ለአርሶ አደሮች እየተከፋፈለ ነው ብሏል፡፡

እንዲሁም ከጥር 24 እስከ የካቲት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ባሉት ቀናት በአምስት መርከቦች 2 ሚሊየን 775 ሺህ ኩንታል ተጨማሪ ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ እንደሚደርስ ይጠበቃል ብሏል።