የሀገር ውስጥ ዜና

የዲራሼ፣ ኩሲሜ፣ ማሾሌ እና ሞሲዬ ብሔሮች የዘመን መለወጫ እየተከበረ ነው

By Meseret Awoke

January 26, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የዲራሼ፣ ኩሲሜ፣ ማሾሌ እና ሞሲዬ ብሔሮች የዘመን መለወጫ በዓል በጋርዱላ ዞን ጊዶሌ ከተማ እየተከበረ ይገኛል፡፡

በበዓሉ አከባበር ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የአጎራባች ዞኖች አመራሮች ተገኝተዋል።

ከአራቱ ብሔሮች የተውጣጡ የፊላ ሙዚቃ ቡድኖች ለ‘ሀይሶት ህርባ’ ዘመን መለወጫ ሙዚቃዊ ትርዒት አቅርበዋል።

ከበዓሉ አከባበር ቀደም ብለው ርዕሰ መሥተዳድሩ በጋርዱላ ዞን ጊዶሌ ከተማ እየተከናወነ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸው ወቅትም በከተማዋ በ400 ሚሊየን ብር የተለያዩ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ለመሥራት ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱ ተገልጿል፡፡

የመጀመሪያው የግንባታ ምዕራፍም በ15 ሚሊየን ብር ተግባራዊ እየተደረገ ነው ተብሏል፡፡

በማስተዋል አሰፋ