የሀገር ውስጥ ዜና

የፓርቲው 2ኛ ጉባዔ ትላልቅ ውሳኔዎች የሚወሰንበት ነው- አቶ አደም ፋራህ

By ዮሐንስ ደርበው

January 27, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በብልጽግና ፓርቲ 2ኛ ጉባዔ ላይ ትላልቅ ውሳኔዎች የሚወሰንበትና ወሳኝ አቅጣጫዎች የሚተላለፍበት መሆኑን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ገለጹ፡፡

አቶ አደም ጠቅላላ ጉባዔውን በሚመለከት ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በማብራሪያቸውም የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ ጉባዔ ከቃል እስከ ባሕል በሚል መሪ ሐሳብ ከፊታችን ጥር 23 እስከ 25 ቀን 2017 በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ገልጸዋል፡፡

ጉባዔ ትላልቅ ውሳኔዎች የሚወሰንበትና ወሳኝ አቅጣጫዎች የሚተላለፍበት መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

ብለጽግና ፓርቲ 15 ነጥብ 7 ሚሊየን አባላት እንዳሉትም በማብራሪያቸው ጠቁመዋል፡፡

በኃይለኢየሱስ ስዩም