የሀገር ውስጥ ዜና

የአፋር ክልል ከ15 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ አልሚዎች ፈቃድ ሰጠ

By ዮሐንስ ደርበው

January 28, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሥድሥት ወራት ከ15 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ አልሚዎች ፈቃድ መስጠቱን የአፋር ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ኃላፊ ኤይሻ ያሲን ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ ለ62 አልሚዎች ፋቃድ ተሰጥቷል፡፡

እነዚህ አልሚዎች 15 ቢሊየን 378 ሚሊየን 635 ሺህ 560 ብር ያስመዘገቡ ናቸው ብለዋል፡፡

ፈቃድ የተሰጠባቸው ዘርፎችም ቱሪዝም፣ ግብርና፣ ኢንዱስትሪ እና ግንባታ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

በሌላ በኩል በተጠናቀቀው ግማሽ የበጀት ዓመት 11 ሺህ 717 የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን ጠቁመዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው