የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ታዬ ከሮክፌለር ፋውንዴሽን ፕሬዚዳንት ጋር መከሩ

By Meseret Awoke

January 28, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከሮክፌለር ፋውንዴሽን ፕሬዚዳንት (ዶ/ር) ራጂቭ ሻህ ጋር ተወያዩ።

በውይይቱ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) በውይይቱ ላይ ተሳትፈዋል።

አብርሃም በላይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ከፋውንዴሽኑ ፕሬዚዳንት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት መደረጉን ገልጸዋል።

በዚህም ነባር ፕሮግራሞች ላይ እንዲሁም ወደፊት ሊኖሩ ስለሚችሉት የአየር ንብረት መቋቋም ኢንሼቲቮች፣ የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ እና የመስኖ ልማት የፋይናንስ እድሎች መዳሰሳቸውን ገልጸዋል፡፡

የሮክፌለር ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ እንደ ኢነርጂ፣ ግብርና እና ጤና ባሉ ፕሮጀክቶች ላይ ድጋፍ የሚያደርግ ዓለም አቀፍ ተቋም ነው፡፡