አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ በሕክምና ማዳን የማይቻሉ ሕመሞችን ስቃይ ለመቀነስ የሚሰጠው አገልግሎት (ፖሌቲቭ ኬር) በ22 ጤና ጣቢያዎች እየተሰጠ መሆኑን የከተማዋ ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡
የቢሮው ም/ሃላፊ ዶ/ር ሙሉጌታ እንዳለ እንደገለጹት÷በሕክምና ማዳን የማይቻሉ ሕመሞች እያደረሱት ያለውን ስቃይ መቀነስ የሚያስችል አገልግሎት ከባለፈው ዓመት ጀምሮ በጤና ተቋማት እየተሰጠ ነው ።
በዚህም 22 ጤና ጣቢያዎችን ከሆስፒታሎች ጋር በማስተሳሰር ዜጎች በጤና ተቋማት አልጋ ይዘው፣ በምልልስ አሊያም ቤታቸው ሆነው አገልግሎቱን እንዲያገኙ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡
ዘርፉ አሰራር ተዘርግቶለት በየጊዜው እየተገመገመ መሆኑን ጠቁመው÷ በተጓዳኝ የሥነ-ልቦና ሕክምና አገልግሎት እየተሰጠ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡
የአገልግሎት ፈላጊዎችን ቁጥር ግምት ውስጥ በማስገባት ሕክምናውን የሚሰጡ ጤና ተቋማትን ቁጥር ለማሳደግ እንደሚሰራም አስረድተዋል፡፡
በመሳፍንት እያዩ