የሀገር ውስጥ ዜና

ምክር ቤቱ ነገ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ሹመትን ያፀድቃል

By Mikias Ayele

January 29, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ በሚያካሂደው መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ሹመትን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ምክር ቤቱ 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ስብሰባውን በነገው ዕለት ያካሂዳል።

በስብሰባው የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እጩ ዋና ኮሚሽነር ሹመትን ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡