አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካ የልማት ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ አይ ዲ) የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚረዱ 2 ሚሊየን 626 ሺህ 780 ብር ዋጋ ያላቸው የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚረዱ ቁሳቁሶችን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለገሰ፡፡
ድርጅቱ የለገሳቸው ቁሳቁሶች የፊት መሸፈኛ ጭምብል፣ የእጅ ጓንት፣ ንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር እና የሙቀት መለኪያ መሆናቸውን ከቦርዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡