የሀገር ውስጥ ዜና

የታንዛኒያው ቻማ ቻ ማፒንዱዚ (ሲ ሲ ኤም) ፓርቲ ዋና ፀሃፊ ኢማኑኤል ኔቼንቤ (ዶ/ር) አዲስ አበባ ገቡ

By Meseret Awoke

January 30, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2017 (ኤፍኤም ሲ) ዋና ፀሃፊው ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዳይሬክተር ጄነራል አምባሳደር ሽብሩ ማሞ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባዔ ከጥር 23 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ “ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

በጉባዔው ከ15 ሀገራት የተውጣጡ የጎረቤት ሀገራት እህት ፓርቲዎች እና የብሪክስ አባል ሀገራት እህት ፓርቲዎች 43 ከፍተኛ አመራሮች እንደሚታደሙ ይጠበቃል፡፡