አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በሁለተኛ ቀን ውሎው በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ እየተወያየ ይገኛል።
ብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤውን ” ከቃል እስከ ባህል ” በሚል መሪ ሀሳብ ከትናንት ጀምሮ እያካሄደ ይገኛል።
የፓርቲው መደበኛ ጉባኤ በጠዋቱ ክፍለ ጊዜው በጉባኤው አዘጋጅ አብይ ኮሚቴ ሪፖርት እና በሁለተኛው ጉባኤ የስብሰባ ሥነ-ሥርዓት ደንብ ላይ ተወያይቶ አጽድቋል።
ጉባኤው በአሁኑ ወቅት በማዕከላዊ ኮሚቴው በቀረበ ሪፖርት ላይ ጥልቅ ውይይት በማድረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን÷ ሪፖርቱን በውይይት አዳብሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።
በቀጣይ መርሐ ግብሩም በቀሪ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ፣ ቀጣይ አቅጣጫዎችንም እንደሚያስቀምጥ የፓርቲው መረጃ ያመላክታል፡፡