የሀገር ውስጥ ዜና

2ኛው ዙር ዓለም አቀፍ የቁርዓን እና አዛን የፍፃሜ ውድድር እየተካሄደ ነው

By Feven Bishaw

February 02, 2025

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የበላይ ጠባቂነት የሚካሄደው 2ኛው ዙር ዓለም አቀፍ የቁርዓን እና የአዛን የፍፃሜ ውድድር በአዲስ አበባ ስታዲዬም እየተካሄደ ነው፡፡

የቁርዓንና አዛን ውድድር የጠቅላይ ምክር ቤት የስራ አስኪያጅ ተወካይ ሼይኽ ኢድሪስ ዓሊ ሑሴን 2ኛው ዙር ዓለም አቀፍ የቁርዓን እና የአዛን ውድድር ስኬት ኢትዮጵያና ልጆቿ ለቁርዓን ያላቸውን ታላቅ ክብር የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

በጠቅላይ ምክር ቤቱ የበላይ ጠባቂነት በዘይድ ኢብኑሳቢት የቁርዓን ማሕበር ጋር የተዘጋጀው ውድድሩ በዛሬው ዕለት ፍጻሜውን ያገኛል፡፡

በአዲስ አብዱልአዚዝ