የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ኦርዲን በድሪ ለጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት አስተላለፉ

By Feven Bishaw

February 02, 2025

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ሆነው በመመረጣቸው የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ሦስተኛ ቀኑን የያዘው የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ከፍተኛ በሆነ ድምጽ የፓርቲው ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል።

ይህንን ተከትሎም የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዲሞክራሲያዊ በሆነ ሂደት ህዝቡን ዳግም ለማገልገል ዕድል ማግኘታቸውን በመጠቆም መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸውም ተመኝተዋል።

በተያያዘ አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና አቶ አደም ፋራህ የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንቶች ተደርገው በከፍተኛ ድምጽ ተመርጠዋል፡፡