የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ አወል አርባ ለብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንቶች የደስታ መልዕክት አስተላለፉ

By ዮሐንስ ደርበው

February 02, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ)የአፋር ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አወል አርባ የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ሆነው በድጋሚ ለተመረጡት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ለተመረጡት የደስታ መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሩ በመልዕክታቸው የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ሆነው በድጋሚ ለተመረጡት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንዲሁም ምክትል ፕሬዚዳንት ለሆኑት አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና አደም ፋራህ መልካም የሥራ ጊዜ ተመኝተዋል፡፡