የሀገር ውስጥ ዜና

ወ/ሮ ዓለሚቱ ለብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት የደስታ መልዕክት አስተላለፉ

By ዮሐንስ ደርበው

February 02, 2025

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ሆነው በድጋሚ ለተመረጡት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ለተመረጡት የደስታ መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡፡

ወ/ሮ ዓለሚቱ በመልዕክታቸው የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ሆነው በድጋሚ ለተመረጡት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንዲሁም ምክትል ፕሬዚዳንት ለሆኑት አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና አደም ፋራህ መልካም የሥራ ጊዜ ተመኝተዋል፡፡