አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጉጂ ዞን ሳባ ቦሩ ወረዳ በባሕላዊ መንገድ ማዕድን በማውጣት ላይ የነበሩ 8 ሰዎች በአፈር መደርመስ አደጋ ሕይወታቸው አለፈ፡፡
አደጋው ትናንት 9 ሰዓት በባሕላዊ መንገድ ማዕድን በማውጣት ሥራ በተሰማሩ ዜጎች ላይ መድረሱን የወረዳው ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አሸናፊ ዳንቆ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡
በአደጋው ለሕልፈት የተዳረጉ ሰዎችን አስከሬን ከተደረመሰው አፈር ውስጥ የማውጣት ሥራ መከናወኑንም አንስተዋል፡፡
በደበላ ታደሰ